ለትንሳኤ በአል መዋያ የሚሆኑ የእርድ እንስሳት ለጸጥታ አባላት ተበረከተ

ጎንደር፤ ሚያዚያ 26/2016  (ኢዜአ)፦በጎንደር ከተማ በሰላም ማስከበር ስራ ለተሰማሩ የፀጥታ አባላት ለትንሳኤ በዓል መዋያ ስጦታ  ተበርክቷል።

በተመሳሳይም በቤንች ሸኮ ዞን ለሚገኙ የፀጥታ አባላትና ለሚዛን ማረሚያ ተቋም የበዓል መዋያ የእርድ እንስሳት በስጦታ  ተበርክቷል።

በጎንደር ከተማ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከንቲባው የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት ዋና አማካሪ አቶ ቻላቸው ዳኘው በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት፤ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችና ባለሀብቶች በከተማው ሰላም ማስከበር ስራ ለተሰማሩ የፀጥታ አባላት የእርድ እንስሳትን በስጦታ አበርክተዋል።

ስጦታው በአንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር ወጪ የተገዙ የእርድ እንስሳት መሆናቸውንም አቶ ቻላቸው ገልጸዋል። 

በዓሉን ምክያት በማድረግ የተደረገው ድጋፍ ህዝባዊ ወገንተኝነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል።  

የፌዴራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ መምሪያ የሻለቃ ምክትል መሪ ኢንስፔክተር እንድሪስ አብዱልጀሊል በበኩላቸው፤ 'ህዝቡ ለበዓል መዋያ ላደረገው ድጋፍ ክብርና ምስጋና አለን ብለዋል፡፡

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይም በቤንች ሸኮ ዞን ለሚገኙ የፀጥታ አባላትና ለሚዛን ማረሚያ ተቋም የበዓል መዋያ የእርድ እንስሳት በስጦታ  ተበርክቷል።

የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን በወቅቱ እንደገለጹት፤ የፀጥታ አካላት ከዞኑ አስተዳደር ጎን በመቆም ለዞኑ ልማትና ዕድገት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም