የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረከበ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረከበ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 26/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረከበ።
ተቋሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ ስፍራዎች እያከናወናቸው ካሉ የግብረ ሰናይ ተግባራት አንዱ የሆነውና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነባቸውን ሶስት መኖሪያ ቤቶች ቁልፍ በዛሬው ዕለት አስረክቧል።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረተዓብ ተክሉ የተገነቡትን ቤቶች ለሶስት አባወራዎች ማስረከባቸውን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የቤቶቹ ግንባታ ወጪ ከ3 ነጥብ 75 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን ተናግረው ድርጅቱ ለዜጎች ያለውን አጋርነት ለመግለጽ በተለያዩ ጊዜያት እና ዘርፎች ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል ብለዋል።
ቤቶቹ በሶስት ወራት ተገንብተው መጠናቀቃቸውን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠቁመው መሰል ማህበራዊ ሀላፊነት የመወጣት ተግባራቱ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የመኖሪያ ቤቶች የተበረከተላቸው ተጠቃሚዎች ድርጅቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ማመስገናቸውንም እንዲሁ በመረጃው ተጠቅሷል።