ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ  ሚያዝያ 26/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬም ቀጥሎ ሲውል ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። 

ከቀኑ 9 ሰዓት ሲዳማ ቡና ከወላይታ ድቻ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሲዳማ ቡና በሊጉ ካደረጋቸው ያለፉት 5 ተከታታይ ጨዋታዎች 2 ጊዜ አሸንፏል። 1 ጊዜ ሲሸነፍ 2 ጊዜ አቻ ወጥቷል።

በነዚህ 5 ጨዋታዎች 5 ግቦችን ሲያስቆጥር 4 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የሚመራው ሲዳማ ቡና በ27 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ተጋጣሚው ወላይታ ድቻ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 1 ጊዜ ብቻ ነው። 2 ጊዜ ሲሸነፍ በተመሳሳይ 2 ጊዜ አቻ ወጥቷል።

ባለፉት 5 ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ 4 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 5 ጎሎችን አስተናግዷል።

በያሬድ ገመቹ የሚሰለጥነው ወላይታ ድቻ በ28 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ሲዳማ ቡና 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፉ አይዘነጋም።

በሌላኛው የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከፋሲል ከነማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ሀድያ ሆሳዕና ካለፉት 5 የሊጉ ጨዋታዎች 2 ጊዜ ሲያሸንፍ 1 ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። 2 ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል።

በ 5ቱ ጨዋታዎች 5 ጎሎችን ሲያስቆጥር 3 ግቦች ተቆጥረውበታል።

በግርማ ታደሰ የሚሰለጥነው ሀድያ ሆሳዕና በ31 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ተጋጣሚው ፋሲል ከነማ ባለፉት 5 የሊጉ ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። 1 ጊዜ ሲሸነፍ 4 ጊዜ አቻ ወጥቷል።

በነዚህ 5 ጨዋታዎች 6 ግቦችን ሲያስቆጥር 7 ጎሎችን አስተናግዷል።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በተያያዘም ትናንት በተደረጉ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮጵያ ቡና ሁለት አቻ ሲለያዩ ኢትዮጵያ መድን ሀምበሪቾን 2 ለ 0 አሸንፏል።

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም