ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት ጥላ ስር የፕሬስ ነጻነትን ትጠብቃለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት ጥላ ስር የፕሬስ ነጻነትን እንደምትጠብቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ መንግስት ለፕሬስ ነጻነት ሁለንተናዊ እድገት እና የስራ ነጻነት ዘርፈ ብዙ አዎንታዊ እርምጃዎችን መውሰዱን ጠቅሷል።

ሆኖም የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን በማስመልከት መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አንዳንድ ኤምባሲዎች በጋራ ያወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ እውነታ በአግባቡ ከግምት ያላስገባ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤምባሲዎቹ በጋራ ያወጡት መግለጫ የሀገሪቱን የሕግ የበላይነት አሳንሶ የሚያይ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት መጠናከር ላይ ገንቢ ሚና የማይጫወት መሆኑን አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም