በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ መድን ሀምበሪቾን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ መድን ሀምበሪቾን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2016(ኢዜአ)፡-በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ መድን ሀምበሪቾን 2 ለ 0 አሸነፈ።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ በ68ኛው እና በ75ኛው ደቂቃ ለመድን የማሸነፊያዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ሦስተኛ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገቡ በ25 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በአንፃሩ ሀምበሪቾ በ8 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በዛሬው የጨዋታ መርሃ ግብር የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ቡና ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።