ፈጥኖ ምርት መስጠት የሚችል የሙዝ ተክል በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ እየለማ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ፈጥኖ ምርት መስጠት የሚችል የሙዝ ተክል በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ እየለማ ነው
ሠመራ፤ ሚያዝያ 25/2016 (ኢዜአ)፡- ፈጥኖ ምርት መስጠት የሚችል የሙዝ ተክል በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ እየለማ መሆኑ ተገለጸ።
በሶስት ወር በሰርቶ ማሳያ ዕድገቱን እንዲጨርስ ተደርጎ ወደ ማሳ ወጥቶ በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የለማው የሙዝ ተክል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በተገኙበት ተጎብኝቷል።
በክልል ደረጃ በተለያዩ ወረዳዎች ሙዝ በስፋት እየለማ መሆኑን ያስታወቁት የክልሉ እንስሳት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኢብራሂም መሐመድ ናቸው።
ከእነዚህ ወረዳዎች ውስጥ ዱብቲ፣ ሐንሩካ፣ ዱለሳ እና አዋሽ ፈንታሌ በዚህ ረገድ የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል።
በክልሉ ለአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ትኩረት በመሠጠቱ ቀደም ሲል ከሶስት ዓመት በላይ ይፈጅ የነበረው ሙዝ በምርምር ተቋማት በመታገዝ ተሻሸሎ የወጣው ዝርያ በአጭር ጊዜ ለምርት መብቃቱን ነው ያስረዱት።
በቀጣይነትም ይህንን በአይሳኢታና አፋምቦ ወረዳዎች አስፍቶ ለማልማት መታቀዱንም እንዲሁ።
ይህ የተጎበኘው የሙዝ ተክል ሳይት በ20 ሄክታር ላይ የለማ መሆኑንም አቶ አብራሂም ተናግረዋል።
ከክልሉ የሙዝ ምርት ከዱለሳ ኤና ሌሎች ወረዳዎች ወደ መሐል አገር ለገበያ እየቀረበ መሆኑ ይታወቃል።