ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባህርዳር ገቡ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2016 (ኢዜአ)፡- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ልዑክ ባህርዳር ገብቷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጣና ሐይቅ ፈርጧ፣ የበርካታ ደሴቶች መናኸሪያ፣ የጢስ አባይ ፏፏቴ መገኛ፣ የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ እና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ በሆነችው ባሀርዳር ከተማ ገብተናል ሲሉ ገልጸዋል።።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ ባህርዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በክልሉ ፕሬዝደንት እና ካቢኒያቸው እንዲሁም የከተማዋ ከንቲባ እና ህዝብ ለተደረገለን አቀባበል ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም