ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መጪውን የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2016(ኢዜአ)፡- የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ ለአቅመ ደካሞችና በዝቅተኛ ኑሮ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚህ ወቅት በስተላለፉት መልዕክት ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው መደጋገፍ የእለት ተእለት ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።


 

መጪውን የትንሳኤ በዓል ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር አብሮ ማሳለፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የወረዳው ነዋሪዎች የትንሳኤ በዓልን ተደስተው እንዲውሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም