ከንቲባ አዳነች አቤቤ መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ከ255 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2016(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ255 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለአቅመ ደካማ የከተማዋ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ በሁሉም ክፍለ ከተሞቻችን እና የከተማ አስተዳደራችን ተቋማት የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ 255 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ እና ለአቅመ ደካሞች በዓሉን በፍሰሀ እንዲያከብሩ ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።

በበጎ ተግባሩ ላይ ለተሳተፉ የከተማዋ ባለሀብቶች ከንቲባዋ ምስጋ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም