ለሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አቀባበል እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2016 (ኢዜአ)፡-ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው በሁለተኛው ምዕራፍ ወደ ሀገራቸው ለመጡ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

ይህንኑ ተከትሎ ዛሬ ማለዳ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እየገቡ ነው።


 

ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና ሌሎች የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች  አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥሪ በመጀመሪያው ምዕራፍ "ከባህላችሁ ጋር ተዋወቁ" በሚል ሃሳብ ተመሳሳይ መርኃ ግብር መካሄዱ ይታወቃል።

ሁለተኛው ምዕራፍ "ከታሪካችሁ ተዋወቁ" በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።

በቀጣይ የሚካሔደው ሶስተኛው ምዕራፍ" አሻራችሁን አኑሩ" በሚል ከሰኔ 2016 እስከ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ተገልጿል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም