ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን በመቀላቀል ድጋፍ አድርገዋል።

የኢዜአ አመራርና ሰራተኞች ተሳትፎውን ያደረጉት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ተደርጎ “ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለውን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ለመደገፍ ነው።


 

ንቅናቄው ለከተማ ውበት እና ለኅብረተሰቡን ጤና መጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑም ድጋፉ ቀጣይነት የሚኖረው ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም