ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ “ፅዱ ጎዳና፤ ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሚየዚያ 23 /2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ “ፅዱ ጎዳና ፤ ኑሮ በጤና” ንቅናቄን የ50 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ተቀላቀለ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ተደርጎ “ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለውን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን በመቀላቀል የ50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።

ንቅናቄው ለከተማ ውበት እና ለኅብረተሰቡን ጤና መጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ያለው የፌዴራል ፖሊስ፤ መላው ህዝብ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም