ለ2016/17 የምርት ዘመን እስከአሁን ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ከውጭ ተጓጉዟል-የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን - ኢዜአ አማርኛ
ለ2016/17 የምርት ዘመን እስከአሁን ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ከውጭ ተጓጉዟል-የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2016 (ኢዜአ):- ለ2016/17 የምርት ዘመን ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስከአሁን ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ከውጭ ተጓጉዞ ጂቡቲ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ 11 ሚሊየን 79 ሺህ 21 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑም ተመላክቷል።
በትላንትናው እለትም 636 ሺህ 600 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የጫነች መርከብ ጂቡቲ ወደብ መድረሷ ተጠቁሟል፡፡
በተመሳሳይ ከ11 ቀናት በኋላ 543 ሺህ ኩንታል ተጨማሪ ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የአፈር ማዳበሪያ ወደብ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።