የሰራተኞችን ጥቅምና መብቶች የማስከበር እንዲሁም ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል - ኢዜአ አማርኛ
የሰራተኞችን ጥቅምና መብቶች የማስከበር እንዲሁም ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፡- የሰራተኞችን ጥቅምና መብቶች የማስከበር እንዲሁም ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ካሣሁን ፎሎ፤ ዓለም አቀፉን የሠራተኞች ቀንን በማስመልከት የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የሰራተኛውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ በየጊዜው የሚነሱ ጥያቄዎችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል።
የሰራተኞችን ጥቅምና መብቶች የማስከበር እንዲሁም ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲረጋገጥ፣ የሥራ ላይ ደህንነት፣ መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
የላቀ ብቃትና እውቀት፣ ክህሎትና ሁሌም ዝግጁነት ያለው ሠራተኛ የማፍራት ስራም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ካሣሁን ፎሎ በበኩላቸው፤ የሠራተኞች መሰረታዊ ጥያቄዎች በሂደት ምላሽ እንዲያገኙ ከመንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በየአመቱ ሚያዝያ 23 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን በነገው እለት በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ135ኛ ጊዜ ይከበራል።