ቀጥታ፡

3ኛው ዙር  የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዛሬ በድሬደዋ ከተማ በይፋ ተጀመረ

ድሬዳዋ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፡- "ኢትዮጵያ ታምርት ፤ እኛም እንሸምት" በሚል መሪ ሐሳብ ለ5 ቀናት በድሬዳዋ ከተማ የሚካሄደው 3ኛው ዙር የአምራች ኢንዱስትሪዎች ዐውደ ርዕይና እና ባዛር በይፋ ተጀመረ።

3ተኛው የኢትዮጵያ ታምርት የድሬዳዋ ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፈትህያ አደንና የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በተገኙበት ነው የተከፈተው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤት የሆኑ ተኪ ምርቶችና በድሬዳዋ የተገጣጠሙ መኪኖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ኢንዱስትሪዎችን አበረታተዋል።

ከ40 በላይ የአምራች ኢንዱስትሪዎችና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተሳተፉበት ዐውደ ርዕዩ ላይ ኢንዱስትሪዎቹ የተለያዩ ተኪ ምርቶቻቸውን ለእይታ አቅርበዋል።

ንቅናቄው በኮሌጆችና ኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።

በኤግዚቢሽኑ ላይ የተለያዩ የፈጠራ ማሽኖችን እና ሌሎች ፈጠራ ውጤቶችን በማቅረብ የተሰማሩት ስራ ፈጣሪዎችም ተሳትፈዋል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም