አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የተመድ ዋና ጸሀፊ ልዩ ተወካይ ካትሪዮና ላይንግ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ልዩ ተወካይ እና በሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ (UNSOM) ኃላፊ ካትሪዮና ላይንግ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅትም አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ድጋፍ ተልዕኮ(ዩኤንሶም) ሀላፊ ካትሪዮና ላይንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለችውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሁለቱ ኃላፊዎች መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም