ቀጥታ፡

ኢዜአ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቋሚነት ለሚያግዛቸው ተማሪዎች ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቋሚነት ለሚያግዛቸው ተማሪዎች ቤተሰቦች የምግብና አይነት ድጋፍ አድርጓል።

በኢዜአ የሴቶችና ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክተር ወይዘሮ ታደለች ቦጋለ እንደገለጹት ተቋሙ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በቋሚነት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

በዛሬው እለትም ተማሪዎቹ የትንሳኤ በዓልን ከወላጆቻቸው ጋር በደስታ እንዲያከብሩ ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።



 

ኢዜአ ከዚህ ቀደም ለ18 ተማሪዎች በቋሚነት ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር አስታውሰው በዚህ ዓመት ተጨማሪ ሁለት ተማሪዎችን በመቀበል ለ20 ተማሪዎች በቋሚነት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ድጋፉ የተቋሙ ሰራተኞች በየወሩ ከደሞዛቸው በፍቃደኝነት በሚያደርጉት መዋጮ መሆኑን በመጥቀስ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከዜና ምንጭነቱ ባሻገር በሌሎች ጉዳዮች ላይም የማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝም ወይዘሮ ታደለች አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም