ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።

በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚመራው ስራ ምክክር እና እርቅ የሰላም ፍላጎታችን እና ተምኔታችን ማጠንጠኛ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህብራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን አዳዲስ ስራዎችን ለመፍጠር እንዳለመች ገልጸዋል።

አረንጓዴ ዓሻራ በመሰሉ ንቅናቄዎች ኃይል ለሁሉም ማዳረስ፣ የዲጂታል ሽግግር እና የተፈጥሮ ከባቢን የመንከባከብ ተግባራትን ለመከወንም ትኩረት ትሰጣለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ለአሀጉሩ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጥሪ ታደርጋለች ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም