በኢትዮጵያ የዲጂታል ንግድ ስርዓት የሚመራበት 'የኢ_ኮሜርስ ስትራቴጂ' ተግባራዊ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የዲጂታል ንግድ ስርዓት የሚመራበት  'የኢ_ኮሜርስ ስትራቴጂ' ተግባራዊ  ሊደረግ ነው።

የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስቴር በብሔራዊ የኢ-ኮሜርስ ስትራቲጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ የባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ እያካሄደ ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂ፤ ዘርፉ የሕግ ማዕቀፍ ኖሮት ተወዳዳሪ ከማድረግ ባሻገር የዲጂታል ኢትዮጵያ ሽግግርን ለማሳለጥ ዓላማ እንዳለው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም