የተለወጠ ማህበረሰብ፣ አካበቢ እና ዜጋ መፍጠር መስዕዋትነትን ይጠይቃል - ዶክተር ለገሰ ቱሉ - ኢዜአ አማርኛ
የተለወጠ ማህበረሰብ፣ አካበቢ እና ዜጋ መፍጠር መስዕዋትነትን ይጠይቃል - ዶክተር ለገሰ ቱሉ
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 21/2016(ኢዜአ)፦ የተለወጠ ማህበረሰብ፣ አካበቢ እና ዜጋ መፍጠር መስዕዋትነትን ይጠይቃል ሲሉ የመንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።
ሚኒስትሩ ህብረተሰቡ ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና ንቅናቄን በመቀላቀል ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ለገሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት እንደገለጹት “ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ የኮሪደር ልማቱ ሌላ ገጽታ ነው።
ይህ ዕቅድ በሀገራችን ከጤና አጠባበቅ እና ምርታማ ዜጋ ከመፍጠር አኳያ መሠረታዊ ለወጥ የሚያመጣ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ለዚህም ትጋት፣ ትዕግስት፣ የተጀመረውን በጊዜው መጨረስ፣ ለቀጣይ ዕቅድ መዘጋጀት፣ያስፈልገናል ብለዋል።
ተቸግረንም ቢሆን በዘመናችን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ስናደርግ ለነገው ትውልድ መሠረት እናስቀምጣለን ያሉት ሚኒስትሩ ህብረተሰቡ በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የቻለውን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል።