ቀጥታ፡

የሸዋል ኢድ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20 /2016(ኢዜአ)፦ የሐረሪ ብሔረሰብ በየዓመቱ የሚያከብረው ባህላዊው የሸዋል ኢድ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል። 

በበዓሉ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጆች እንዲሁም የአጎራባች ክልል ሕዝቦች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። 

የሸዋል ኢድ በዓል በማይዳሰስ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ ትምህርት እና ባህል ድርጅት/ UNESCO የተመዘገበ አምስተኛ የኢትዮጵያ ቅርስ መሆኑ ይታወቃል። 

ኢትዮጵያ ካሏት ደማቅ ማህበራዊ እሴቶች ውስጥ አንዱ የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሀገሪቱ የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር እና መልካም ገፅታን በመገንባት ረገድ ፋይዳው የላቀ ነው።

የክልሉን የቱሪዝም ማዕከልነት የሚያሳድገው ከመሆኑ ተጨማሪ የህዝብ ተጠቃሚነትን ከማሳደግ አንፃር ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም