የሚሰሩ እጆችን ከስራ እያገናኘን፣ የሚፈጥር አዕምሮን ወደ ተግባር እያስገባን የተሻለ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየሰራን ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

80

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ የሚሰሩ እጆችን ከስራ እያገናኘን፣ የሚፈጥር አዕምሮን ወደ ተግባር እያስገባን የተሻለ የስራ ዕድል ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ውይይት በማድርግ ወደ ላቀ ደረጃ የተሸጋገሩ አምራቾችን መሸለማቸውን ገልጸዋል።


 

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ኢትዮጵያ-ታምርት፤ እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ሃሰብ በተቀናጀና ቀጣይነት ባለው የድጋፍ ማዕቀፍ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ በተዘጋጀ የንቅናቄ ማጠቃለያ መድረክ ላይ መገኘታቸውን ጠቁመዋል።

ከንቲባ አዳነች የሚሰሩ እጆችን ከስራ እያገናኘን፣ የሚፈጥር አዕምሮን ወደ ተግባር እያስገባን ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያነሷቸውን ቅሬታዎች በመፍታት የተሻለ የስራ ዕድል ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለንም ብለዋል።


 

ባለው የድጋፍ ማዕቀፍ በፍትሃዊነት እያስተናገድን፣ የሚቀሩትን በጋራ ጥረት እያሟላን የኢንዱስትሪ ዘርፉን የማምረት አቅም እያሻሻልን እና የሚነሱ ቅሬታዎችን በጋራ እየቀረፍን ለወጣቶቻችን በቂ የስራ እድል የሚፈጥር የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንገነባለን ሲሉም ገልጸዋል በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም