አትሌት መዲና ኢሳ በ5 ኪሎ ሜትር ከ20 ዓመት በታች የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

181

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ የአዲዳስ ኩባንያ ባዘጋጀው አዲዜሮ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር ጭምር አሸነፈች፡፡

የ19 ዓመቷ አትሌት መዲና ርቀቱን 14 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር ያሸነፈችው፡፡

በዚሁ ውድድር አትሌት መልክናት ውዱ ሁለተኛ እንዲሁም ፎቲየን ተስፋይ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በወንዶች ዮሚፍ ቀጀልቻ በ13 ደቂቃ በመግባት ሲያሸንፍ ይሁኔ አዲሱ በ5 ሴኮንዶች ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም