የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

94

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2016(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸማችንን እየገመገምን ነው ብለዋል፡፡


 

በግምገማ መድረኩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የህዝባችንን የኑሮ ጫና ለማቅለል እና የተጀመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶቻችንን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ አዳጊና ተደማሪ የሆኑ አዳዲስ እይታዎችን ተግባራዊ በማድረግ፣ ውጤታማ የስራ ባህል በመከተል እንዲሁም የአመራር ቅንጅትን ይበልጥ በማጎልበት የተከተልነው መንገድ ውጤታማ ያደረገን ነበር ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ክፍተቶቻችንን በመሙላት ለህዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር ለማዋል የምንሰራ ይሆናል ማለታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም