በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ በአካባቢው የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ለመመልከት ኮምቦልቻ ገባ

74

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2016(ኢዜአ)፡- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የፌደራል መንግሥት እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በአካባቢው የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ለመመልከት ኮምቦልቻ ገብቷል፡፡

ልዑኩ ኮምቦልቻ ከተማ ሲደርስ በአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና በከተማው ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ በቆይታችን በአካባቢው የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን የምንጎበኝ ይሆናል ብለዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በኮምቦልቻ በሚኖራቸው ቆይታ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን እንደሚመለከቱ ይጠበቃል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራው ልዑክ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም