ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገሃር መኖሪያ መንደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክትን አስጀመሩ

114

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገሃር መኖሪያ መንደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክትን በይፋ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የጊፍት ሪል ስቴት አመራሮች ተገኝተዋል።


 

በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የተገለጸው ይህ የግንባታ ፕሮጀክት የሚከናወነው በከተማ አስተዳደሩና በጊፍት ሪል ስቴት ትብብር ነው።

አጠቃላይ በፕሮጀክቱ 12 ሺህ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች የሚገነቡ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 4 ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡ ተገልጿል።

ከሚገነቡት ቤቶች ውስጥም 3ሺህ540 ለመኖሪያ 460ዎቹ ደግሞ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም