ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተመለሰ

128

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 18/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል። 

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 22ኛ ሳምንት ምድብ ሀ ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ጀምረዋል።

በዚሁ ምድብ ኦሮሚያ ፖሊስና ጅማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ መለያየታቸውን ተከትሎ የምድቡ መሪ የሆነው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምስት ጨዋታ እየቀረው ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መመለሱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ2015 ዓ.ም የውድድር ዘመን ከፕሪምየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ የሚታወስ ሲሆን በዓመቱ ወደ ፕሪሚየር ሊግ መመለሱን አረጋግጧል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ ለ አርባ ምንጭ ከተማ እየመራ ሲሆን የምድቡ አሸናፊ ከሆነ እንደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዓመቱ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ዳግም የሚመለስ ይሆናል።

ከ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት አንስቶ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚገኙ ሁለት ክለቦች ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲያድጉ ሁለት ክለቦች ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊጉ እንዲወርዱ መወሰኑ ይታወቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም