የህንድ መንግሥት ባደረገው ድጋፍ  ለ400 ስዎች የሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ የተሐድሶ አገልግሎት በሎጊያ ሆስፒታል  እየተሰጠ ነው

86

ሠመራ ፤ ሚያዝያ 18/2016  (ኢዜአ)፦የህንድ መንግሥት ባደረገው ድጋፍ  ለ400 ሰዎች የሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ የተሐድሶ አገልግሎት በሎጊያ ሆስፒታል እየተሰጠ ነው።  

በሰው ሰራሽ የተሃድሶ አገልግሎት አሰጣጥ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የአፋር ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አሊ መሐመድ እንዳሉት በፕሮጀክቱ የተጀመረው ለአካል ጉዳተኛ ወገኖቻችን ሰው ሰራሽ አካል መሥጠት ዜጎቹ በነፃነት ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።

ከዚህም በተጓዳኝ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግር ሚና ያለው መሆኑን ጠቅሰው የህክምና ባለሙያዎችን አቅም ከማጠናከር ባሻገር ለተቋማት መጠናከር ወሳኝ ነው ብለዋል።

በዚህ ዘመቻ አገልግሎቱን የሚያገኙ ወገኖችን ወደ አዲስ ምዕራፍ  ያሻገረ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ መሣካት ድጋፍ ያደረገው የህንድ መንግስት እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዲሁም የሠመራ ዮኒቨርሲቲን አመሥግነዋል።

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶክተር  መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ይህ ዕለት ለተከታታይ ጊዜያት የተደረጉ ጥረቶችን በተጨባጭ ያየንበት እና ምርታማ የሆንበት በመሆኑ የህንድ መንግስት ሊመሠገን ይገባዋል ብለዋል።

400 የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ ለማድረግ ክልል ደረጃ መጥተው ልምዳቸውን ዕውቀታቸውንና ሰብአዊ አገልግሎት በመለገሳቸው አመሥግነዋል።


 

ይህ ኘሮጀክት የሰብአዊነት ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው  በዚህ መሠረት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በኩል አፋርን ተደራሽ ማድረግ ምርጫ  መሆኑን ጠቅሰው ይህ ጅማሬ እንጂ መጨረሻ እንዳልሆነ አያይዘው አምባሳደሩ ተናግረዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ የሆኑት አቶ አሳልፈው አህመዲን  ይህ ኘሮግራም ለተከታታይ ሁለት ወራት የሚቆይ መሆኑን ገልፀዋል።

የአካል ድጋፍ   መሠረታዊ ፍላጎት በመሆኑ  ይህን በማሟላት  የዜጎቹን አምራችነት  ተሳትፎ መጨመር ማሳደግ እንደሚገባ እስረድተዋል።

በአሁኑ ዘመቻ የሚሰጠው ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፉ የ10 ሚሊዮን ብር ግምት እንዳለውም ተናግረዋል።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ ወይዘሮ ፋጡማ መሐመድ በበኩላቸው የክልሉ ነዋሪዎች ይሄን ዕድል ለማግኘት በተለያዩ አጎራባች ክልሎች ሲሄዱ እንደ ነበር ተናግረዋል።

ዛሬ ላይ ክልሉ ድረስ መጥተው አገልግሎቱ እንዲሰጥ ያደረጉትን የህንድ መንግስት፣የፌዴራል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴርና የሠመራ ዩኒቨርሲቲን አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም