በአፍሪካ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በይፋ ስራ ጀመረ

115

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- በአፍሪካ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በይፋ ስራ ጀመረ።

ኢኒሼቲቩ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አነሳሽነት በአፍሪካ በተለይ ኢንቨስትመንትን፣ ስራ ፈጠራንና ስታርትአፕን ለመደገፍ የሚሰራ ነው።

ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በአህጉሪቱ ግዙፍ የፓንአፍሪካ ስታርትአፕ ምህዳር መፍጠርን ያለመ ነው።


 

በኢንሼቲቩ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ታዬ፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ባሳለፍነው ጥር ወር በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በመሆን ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

ኢኒሼቲቩ 1 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በማሰባሰብ የ100 ሚሊዮን አፍሪካውያንን ህይወት ለማሻሻልና ለ10 ሚሊዮን ሰዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ አስቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም