የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ፦

140

የወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ

👉 ለኢንደስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ፤

👉 በወጪ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በማበረታታት ረገድ የታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ እና የዘርፉን ተዋንያን የሚያበረታታ ሥርዓት

በመዘርጋት ተወዳዳሪነት ማላቅ ይቻል ዘንድ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ተደርጓል።

የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ ደንብን በተመለከተ፦

👉 ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፤

👉 የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያወጣውን ወጪ በከፊል መሸፈን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

የጤና ፖሊሲን በተመለከተ

👉 በስራ ላይ ያለው የጤና ፖሊሲ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት ቆይቷል፤

👉 ፖሊሲው በጸደቀበት ወቅት ከነበረው ጠቅላላ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ፤

👉 እየተከሰቱ ያሉ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መበራከት፤

👉በሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና ዙሪያ የሚከሰቱ ለውጦች፤

👉 ዘርፉ ጥራት እና ፍትሀዊነት ያለው አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ችግሮች የሚስተዋሉበት በመሆኑ፤

👉 እንዲሁም ከሀገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር የሚጣጣም የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ፖሊሲው ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

በግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲን በተመለከተ

👉 በስራ ላይ የነበረው የግብርና ፖሊሲ ከአዳጊ የምርትና ምርታማነት ፍላጎት ጋር አብሮ መጓዝ የቻለ ባለመሆኑ፤

👉 ለግብርናው ዘርፍ እድገት ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን መለወጥ አስፈላጊ በመሆኑ እንዲሁም ሀገራችን ከምትከተለው ብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ስርአት ጋር የሚጣጣም ፖሊሲ ማስፈለጉ ታምኖበታል፤

👉 ስለሆነም የግብርና ዘርፍን ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር የበለጠ የሚያስተሳስር፣

👉 የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅና በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችል፤

👉 የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም በገጠር መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት የሚያግዝ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም