የኢዜአ ባልደረባ የወይዘሪት ውዳላት አየነው የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ

89

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- በትናንትናው እለት ያረፈችውና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ባልደረባ የነበረችው ወይዘሪት ውዳላት አየነው የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በቀጨኔ መድኃኒዓለም ዘላቂ ማረፊያ ተፈጽሟል።

ወይዘሪት ውዳላት አየነው ከመጋቢት 2008 ዓ.ም ጀምሮ በደንገተኛ ህመም ህይወቷ እስካለፈበት ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሰርታለች።

ለቤተሰቦቿ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው ወይዘሪት ውዳላት አየነው፤ ከአባቷ አቶ አየነው አብደላ እና ከእናቷ ወይዘሮ አበበች አሊ በ1973ዓ.ም በአዲስ አበባ ነበር የተወለደችው።

ወይዘሪት ውዳላት ኢዜአን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ መስራቷን የስራ ማህደሯ ያስረዳል።

ኢዜአ በወይዘሪት ውዳላት አየነው ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም