በምስራቅ ወለጋ ዞን መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ ከሽብር ቡድኑ በርካታ መሳሪያ መማረኩ ተገለጸ

131

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016(ኢዜአ)፦ በምስራቅ ወለጋ ዞን በሲቡ ሲሬ ወረዳ አገሎ ተለማና ኮምሳ በተባሉ ቦታዎች እንዲሁም በዞኑ ዋዩ ጡቃ ወረዳ በልዩ ስሙ መኮ በተባሉ ቦታዎች ለቀናት በተደረጉ ዘመቻዎች በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን በማዕከላዊ ዕዝ የክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አባይነህ አስማማው ገለጹ።


 

ኮሎኔል አባይነህ እንደገለጹት የሽብር ቡድኑ አሁን ላይ የሰራዊቱን ምት መቋቋም ተስኖት ሙት እና ቁስለኛ ከመሆን ባሻገር እየተማረከ ሲሆን 17 የሸኔ ታጣቂም ተገድሏል።


 

በዚህ ዘመቻ የተማረከ ክላሽ 19፣ መትሪየስ 01 እና በርካታ ተተኳሾች በክፍለ ጦሩ ሠራዊት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም