ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የባህል ስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ መልካም ዕሴቶችን ለመገንባት ላደረጉት ጥረት አመሰገኑ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የባህል ስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ መልካም ዕሴቶችን ለመገንባት ላደረጉት ጥረት አመሰገኑ
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- ከመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የባህል ስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ መልካም ዕሴቶቻችንን ለመገንባት ላደረጉት ጥረት እናመሰግናለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው 21ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 17ኛው የባህል ፌስቲቫል ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝቱን አስመልክተው ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የልኡካን ቡድኑ ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ያለውን የስፖርት ማዘውተሪያዎችን እና የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከላትን በማቋቋም ባለተሠጥዖ ወጣቶችን ከራዕያቸው ጋር ማገናኘት የሚያስችል የትውልድ ግንባታ ስራን እና ለዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድር ማካሄጃ እየተሰራ ያለውን የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየምን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡