የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አባላት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

75

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክር ቤት አባላት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን እንቅስቃሴ እየጎበኙ ነው።

የምክር ቤት አባላቱ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ በአምስት የኮሪደር ልማት መስመሮች ተዘዋውረው ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

ከኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ባሻገርም ለልማት ተነሺ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ያረፉባቸውን መኖሪያ ቤቶችንም ጎብኝተዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም