የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካሜሩን ዱዋላ ከተማ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ አሳደገ

76

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካሜሩን የንግድና የኢኮኖሚ ማዕከል ወደ ሆነችው ዱዋላ ከተማ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 11 ማሳደጉን ገለጸ።

በዚህም ከግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በረራውን ወደ 11 ከፍ እንደሚያደርግ ነው ያስታወቀው።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማዋ 7 ሳምንታዊ በረራዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም