የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

110

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፡- የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አል-ዳባይባ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ምሽቱን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም