ኢትዮጵያ እና ስሎቬኒያ የፖለቲካ ምክክር አደረጉ

97

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ እና ስሎቬንያ መካከል የፖለቲካ ምክክር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተካሂዷል።

በምክክሩ የሁለቱን አገሮች ወቅታዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት መገምገሙንና ሀገራቱ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማሳደግ እንዲሁም በወቅታዊ አለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት መሆኑ ተገልጿል።

የፖለቲካ ምክክሩን በኢትዮጵያ ወገን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘነበ ከበደ በስሎቬንያ በኩል ደግሞ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና የአውሮፓ ጉዳዮች ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ማያ ኖርቺች ስታምካር መምራታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም