ኢትዮጵያ 4ኛው አለም አቀፍ የፋይናንስ የልማት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ቁርጠኛ ናት - አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ 

199

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ በመጪው ሃምሌ የሚካሄደውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 4ኛው አለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ገለፁ።

አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሀመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅት አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ፤ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 4ኛውን የፋይናንስ ልማት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በመንግስታቱ ድርጅት መካከል ስላለው ዘርፈ-ብዙ አጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ተገልጿል።

በተጨማሪም በዘላቂ የልማት ግቦች የትግበራ ሁኔታ፣ በመጪው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እና በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይም ውይይት ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም