ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት አውደ ርዕይና ባዛር በአዲስ አበባ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት አውደ ርዕይና ባዛር በአዲስ አበባ ተከፈተ
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፡- "ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት" ከተማ አቀፍ አውደ ርዕይና ባዛር ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል።
አውደ ርዕይና ባዛሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ በይፋ ከፍተዋል።
በአውደ ርዕይና ባዛሩ ከ200 በላይ አምራች ኢንደስትሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን ፤ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ ማኅበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገዛበት እና የገበያ ትስስር የሚፈጥርበት ይሆናል ተብሏል።
በጊዮን ሆቴል የተከፈተው ይህ አውደ ርዕይና ባዛር ከዛሬ ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ጀምሮ ለአራት ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል።