ቀጥታ፡

የኢትዮ-ጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚቴ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮ-ጅቡቲ 16ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚቴ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በጅቡቲ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በግምገማ መድረኩ በትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የተመራው ልዑካን ቡድን የኢፌዲሪ  ገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እና የጅቡቲ የመሠረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሁማድ ተገኝተዋል።


 

ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) መድረኩ በ16ኛው የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች እንዲሁም ከስምምነቱ በኋላ በተከሰቱ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት የትብብር ማዕቀፎች፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና በጠረፍ ንግድ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በዲኪል ጋላፊ መንገድ ግንባታ መጓተት ዙሪያ እና በመሰል ነጥቦች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ በጅቢቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም