በትግራይ ክልል የኩፍኝ በሽታና የልጅነት ልምሻ ፖሊዮ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

76

ሸሬ እንዳሰላሴ፤ሚያዝያ 15 /2016 (ኢዜአ)፦በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች የቤት ለቤት የኩፍኝና የልጅነት ልምሻ ፖሊዮ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው።

በክልሉ ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የክትባት መርሃ ግብሩን ዛሬ በይፋ ያስጀመሩት በጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ሰሜናዊ  ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ አቶ እልፍዮስ ታደሰ እንደገለፁት፤ ክትባቱ ለቀጣዮቹ ስድስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

ሁሉም ህፃናት እንዲከተቡ የማድረግ ስራም በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አቶ እልፍዮስ አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም የተከተቡ ህፃናትም የመርሃ ግብሩ አካል የተደረጉ መሆኑን ገልፀው በዘመቻው በዞኑ ከ20 ሺህ በላይ ህፃናት እንደሚከተቡም አስረድተዋል። 

የክትባት ዘመቻው በክልሉ ከሚያዝያ 15 እስከ ሚያዝያ 20/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የታወቀ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ክትባቱ ይሰጣል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም