የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጭው መስከረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ

99

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጪው መስከረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ "ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን - አጀንዳ 2063" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጭው መስከረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል ብለዋል።

ዛሬ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሄራዊ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ የመክፈቻና የግንዛቤ መስጫ መድረክ መካሄዱንም ጨምረው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ታሪካዊት፣ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ህብረት መስራች ሀገር ይህንን ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።

በመሆኑንም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክ ለማዘጋጀት የተሰጣትን አፍሪካዊ ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ ተግባብተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም