የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመሪነት ሚናው ፡-

98

    75 ዓመታትን በስኬት የተጓዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚው የአቬዬሽን ግሩፕ ነው፤

    አየር መንገዱ 63 የአፍሪካ ከተሞችን ጨምሮ በየቀኑ ወደ ተለያዩ የአለም ክፍሎች በርካታ በረራዎችን ያደርጋል፣

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የትስስር ሚናው ከየትኛውም አየር መንገድ በላይ በአህጉሩ በረራ ያደርጋል፣

    አየር መንገዱ በ5 አህጉሮች በ58 መዳረሻዎች በ100 አለም አቀፍ በረራዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፤


     ይህም በቱሪስቶቸ ተመራጭ የሆኑትን የአፍሪካ ስፍራዎች አዲስ አበባ፣ ዛንዚባር፣ ኪሊማንጃሮና ሲሼልስን በዋናነት ያካተተ ነው፤

    በዚህም ከስካይ ትራክስ ለ5 ዓመታት ተከታታይ ስኬት ያስመዘገበ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ በመባል ባለ 4 ኮከብ ሽልማት ተበርክቶለታል፤ 


    በቀውስ ወቅት የላቀ የአመራር ስኬት ደግሞ በ2020 ሽልማት ተብርክቶለታል፤

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ፣ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያ ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎቸም የአለም ክፍሎች በምቹ በረራው እያገለገለ ይገኛል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም