ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የደቡብ ግንባር ሆስፒታል የግንባታ ሂደቱን ጎበኙ

92

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016 (ኢዜአ)፡- የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በኦሮሚያ ክልል ብሻን ጉራቻ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የደቡብ ግንባር ሆስፒታል የግንባታ ሂደቱን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የሆስፒታሉን የግንባታ ሂደትና አሁን ላይ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ በተቋራጩ አማካኝነት ሰፊ ገለፃ ተደርጓል፡፡

የሆስፒታሉ ግንባታ ከተጀመረ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም አሁን ያለበት የግንባታ ደረጃ ጥሩ የሚባልና በተፈለገው ልክ እየሄደ መሆኑን ገልፀው ግንባታው በተቀመጠለት ጊዜ መጠናቀቅ እንዳለበት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አሳስበዋል፡፡


 

በጉብኝቱም የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼን ጨምሮ የደቡብ ዕዝና የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዦች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም