በአዳማ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ84 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል

65

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፦ በአዳማ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ84 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ።

የአዳማ ከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ጠይብ፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 84 ሺህ 139 ዜጎች በተለያዩ መስኮች ወደ ስራ መሰማራታቸውን ተናግረዋል።

1 ሺህ 344 ሼዶች በህዝብ ተሳትፎ ተገንብተው የስራ እድል ለተፈጠረላቸው ወጣቶች መተላለፋንም እንዲሁ።

ስራ አጥ ወጣቶቹ ዶሮና ከብት እርባታን ጨምሮ በኢንዱስትሪ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች የተሰማሩ መሆኑን ገልጸዋል።

የዶሮ መኖ የሚያመርቱት ስድስት ማህበራትን በማደራጀት ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የስራ እድል ለተፈጠረላቸው ዜጎች የመስሪያ ቦታ፣ የገበያ ትስስር እና የመሸጫ ቦታዎችን የማመቻቸት ስራ መከናወኑንም ጠቁመዋል።

በከተማዋ በግብርና ዘርፍ የተደራጁ ወጣቶች የሚያቀርቡት ምርት የኑሮ ውድነትን ከመቀነስ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውንም አመልክተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም