15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ አዲስ አበባ ገቡ

126

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- 15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ አዲስ አበባ ገቡ። 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ- ጉባኤ ወይዘሮ ዘሐራ ሁመድ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሀሰን አብዱልቃድር (አምባሳደር)፣ የቀድሞ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እስማኤል አሊስሮ፣ የቀድሞው ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሀሰን አብደላ(አምባሳደር)፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። 

የእውቁ ሱልጣን አሊሚራህ ልጅ የሆኑት 15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ የመላው አፋር ሱልጣን የነበሩት ወንድማቸው ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ ማረፋቸውን ተከትሎ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ነበር የተሾሙት።

በዛሬው ዕለትም ከውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል።

ለብዙ ዘመናት የአፋር ሱልጣን መሪዎች በመላው አፋር ህዝብ ዘንድ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በባህላዊ ስልቶች በዘላቂነት በመፍታት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ይነገራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም