ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ ጎበኙ

150

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 14/2016 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ ትናንት ምሽት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን የሚያዘምንና ተወዳዳሪነቷን የሚያረጋግጥ ከመሆኑ ባሻገር የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስፋት የከተማዋን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳደግ ይጠበቃል፡፡

የልማት ስራዎቹ የንግድ ማዕከላት፣ የባስ እና ታክሲ ተርሚናሎች፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች፣ የህጻናት መጫወቻ፣ መጸዳጃ ቤቶች እና ፓርኪንጎችን የሚያካትቱ መሆኑም ይታወቃል።


 

አሁን ላይ የኮሪደር ልማቱን በተያዘለት ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌት እየተሰራ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ትናንት ምሽት የስራውን ሂደት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በቅርቡ የፌዴራል እና የክልሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የኮሪደር ልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት በሰጡት ማብራሪያ የኮሪደር ልማቱ ጠንካራ የተቋማት ቅንጅት የታየበትና ቀን ከሌሊት የሚሰራ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም