በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቡና ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

207

ዲላ፤ ሚያዝያ 14/2016 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተሻሻሉ የቡና ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርኃ  ግብር በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙያ ወረዳ ጎላ ቀበሌ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም  ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ብሩ ለኢዜአ እንዳሉት ክልላዊ የቡና ችግኝ ተከላ መርኃ ግብር እየተሄደ ነው።

በክልሉ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቶን በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያን ለቡናው ችግኝ ተከላ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

በተያዘው ዓመት ከ35 ሚሊዬን በላይ የተሻሻሉ የቡና ችግኞች በክልሉ ለተከላ መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው፤ ከ32 ሚሊዬን የሚልቀው በተያዘው ሚያዝያ ወር የሚተከል መሆኑን ተናግረዋል።


 

በክልሉ ያረጁ የቡና ተክሎችን በተሻሻሉ ዝሪያዎች መተካትን ጨምሮ የተለያዩ የምርታማነት ማሻሻያ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህም በሄክታር ሰባት ነጥብ አራት ኩንታል የሆነውን የክልሉን አማካይ የቡና ምርታማነት በቀጣይ ዓመት ወደ ዘጠኝ ኩንታል ለማሳደግ ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተከላው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የክልሉ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፀሐይ ወራሳን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም አርሶ አደሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም