በቬና በተካሄደ የማራቶን ውድድር አትሌት ጫላ ረጋሳ በአንደኝነት አጠናቀቀ

267

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- በቬና የተካሄደውን የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ጫላ ረጋሳ አንደኛ በመወጣት አጠናቀቀ፡፡

አትሌት ጫላ ረጋሳ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት አሸንፏል።

በለንደን ማራቶን ደግሞ ትዕግስት አሰፋ እና ቀነኒሳ በቀለ ውድድራቸውን በተመሳሳይ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያ አሸናፊዎች ሆነዋል።

የሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ዛሬ በተደረገው በ44 ኛው የለንደን ማራቶን በ 2ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሁለተኛ ደረጃ ውድድርዋን አጠናቃለች።

በወንዶች ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ውድድርን በ2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ15 ሰኮንድ በሁተኝነት በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል።

በለንደን የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት መገርቱ አለሙ በ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ34 ሰኮንድ 4ኛ፣ አትሌት ትዕግስት ከተማ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ 7ኛ፣ አትሌት ያለምዘርፍ ይሁአለው 2 ሰዓት ከ 23 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ 8ኛ እንዲሁም አትሌት ፅጌ ሀይለስላሴ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል።

እንዲሁም አትሌት ክንዴ አተናው በ2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ 8ኛ ደረጃን ይዞ በመግባት ውድድሩን አጠናቋል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ውድድር የገባበት ሠዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ ሲመዘገብ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለጽ የዓለም አትሌቲክስ አድናቆት መግለጹን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም