የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል

56

ሀዋሳ፤ ሚያዚያ 12/2016 (ኢዜአ)፡- በሌማት ትሩፋት መርሃግብር በተከናወኑ ተግባራትና የመጡ ለውጦች ላይ የሚመክር ሀገራዊ የምክክር መድረክ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

በመድረኩ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮቹ ወደ ሀዋሳ ከተማ የገቡ ሲሆን በቆይታቸው በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የተከናወኑ ሥራዎችን አፈጻጸም ይገመግማሉ።

የሌማት ትሩፋት መርሀግብር በእንስሳትና አሣ ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንዲቻል የተቀረጸ ሲሆን መርሃ ግብሩ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል።

መርሃ ግብሩ በዋናነት እንቁላል፣ ዶሮ፣ ማር፣ ወተት እና አሣ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የልማት መስኮች ናቸው።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም